የቆላማ አካባቢ የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት በኑዌር ብሔረሰብ ዞን ማኩዌይ ወረዳ በ10 ሚሊዮን ብር ወጪ ያስገነባዉን የእንስሳት ህክምና ክሊኒክ አሰመረቀ።
የእንስሳት ህክምና ክሊኒክ የምርቃ ስነ-ስርዓት ላይ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ጋትሉዋክና የጉባኤ አባላት በተገኙበት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።
ጋምቤላ ብዙሃን መገናኛ አገልግሎ (መጋቢት 22/2017 ዓ.ም
****
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ጋትሉዋክ በጉብኝቱ ወቅት እንዳሉት ዞኑ ከፍተኛ የእንስሳት ሀብት ያለበት ቢሆንም ከዘርፉ ማግኘት የሚገባዉን ጥቅም እንዳላገኘ ገልጸዋል።
የእንስሳት ህክምና ክሊኒኩ የእንስሳት ጤንነት ለመጠበቅ አስፈላጊ መሆኑንም ተናግረዋል።
ህብረተሰቡ በከፍተኛ ወጭ የተሰራዉን የእንስሳት ህክምና መስጫ ክሊኒክ እንደራሱ ንብረት መጠበቅ እንዳለበትም ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል።
የቆላማ አካባቢ የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ኃላሪ ዶክተር ቤል ቢቾክ በበኩላቸው ፕሮጀክቱ ስድስት ወር ባልሞላ ጊዜ ዉስጥ የወረዳዉን ህዝብ ተጠቃሚ የሚያደርግ የእንስሳት ክሊኒክ ሰርቶ ለአገልግሎት ክፍት ማድረጋቸዉን ገልጸዋል።
በተጨማሪም ፕሮጀክቱ በዚሁ ወረዳ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እያስገነቡ መሆኑን ገልጸዉ ባጠረ ጊዜ ዉስጥ አጠናቀዉ እንደሚያስረክቡ ተናግረዋል።
ፕሮጀክቱ ከዚህ ቀደም በሌሎች ወረዳዎች እና ዞኖች የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚ የሚያደርግ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ሰርተዉ ማስረከባቸዉን ዶክተር ቤል ገልጸዋል።
የእንስሳት ህክምና ክሊኒኩ በክልሉ ሶስተኛ መሆኑንም ተናግረዋል።
ፕሮጀክቱ የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ እንደሚገኝ የገለጹት ዶክተር ቤል ህብረተሰቡ የተሰራዉ ፕሮጀክት ላይ በአግባቡ መጠቀም እንዳለበትም ተናግረዋል።